am_tn/psa/030/001.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ተጓዳኝ ሐሳብ በዕብራይስጥ ቅኔ የተለመደ ነው

በቤተ መቅደሱ ምረቃ ጊዜ የተዘመረ

‹‹ይህ መዝሙር የተዘመረው ቤተ መቅደሱ የተመረቀ ጊዜ ነበር››

የዳዊት መዝሙር

ይህም ማለት 1) መዝሙን የጻፈ ዳዊት ነበር፣ ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) መዝሙሩ በዳዊት አዘማመር ስልት ነው፡፡

አንሥተኸኛልና

እግዚአብሔር እርሱን መታደጉና ከሞት ማዳኑ እርሱን ከጥልቅ ጉድጓድ ማውጣት እንደሆነ ጸሐፊው ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ ታደግኸኝ››

ነፍሴን ከሲኦል አወጣት

‹‹ሲኦል›› የሞቱ ሰዎች የሚሄዱበት ስፍራ ስለሆነ ሞትን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከሞት አዳነኝ››

ነፍሴን አወጣት

‹‹ነፍሴ›› የሚለው የሚያመለክተው ጸሐፊውን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አወጣኝ››

ወደ መቃብር ከመውረድ

‹‹መቃብር›› ሞትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከመሞት››