am_tn/psa/028/006.md

1.8 KiB

የልመናዬን ድምፅ ሰምቷል

እዚህ ላይ፣ ‹‹ድምፅ›› ጸሐፊው የተናገረውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱን ስለምን የተናገርሁትን ሰማ››

ያህዌ ብርታቴ ነው

‹‹ብርታት›› የሚለውን የነገር ስም፣ ‹‹ብርቱ›› በማለት መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ብርቱ ያደርገኛል››

ጋሻዬ

ይህ የሚያመለክተው ያህዌ ጸሐፊውን ይጠብቀው እንደ ነበር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ ይጠብቀኛል››

ልቤ ይታመናል

‹‹ልብ›› መላውን ሰው ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እታመናለሁ››

ተረዳሁ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ ረዳኝ››

ልቤ ሐሤት አደረገ

‹‹ልብ›› መላውን ሰው ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጣም ደስ አለኝ››

ያህዌ ለሕዝቡ ብርታታቸው ነው

‹‹ብርታት›› የሚለውን የነገር ስም፣ ‹‹ብርቱ›› በማለት መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ሕዝቡን ብርቱ ያደርጋል››

ለቀባውም የመዳን ዐምባ ነው

ያህዌ ንጉሡን በሰላም መጠበቁ ያህዌ ንጉሡ ሄዶ የሚሸሸግበት ቦታ እንደ ሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ ንጉሥ እንዲሆን የቀባውን በደህና ይጠብቀዋል››

ለቀባው

ይህ የሚያመለክተው ንጉሡን ነው፡፡