am_tn/psa/028/003.md

2.4 KiB

አታርቀኝ

እግዚአብሔር ሰዎችን መቅጣቱ እነርሱን ማራቅ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ በዚህ ምሳሌያዊ ቋንቋ ያህዌ ወደ እስር ቤት፣ ምርኮ ወይም ሞት እያራቃቸው እንደሆነ ሊያመለክት ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አታስወግደኝ››

ከባልንጀሮቻቸው ጋር ሰላም ከሚናገሩ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ባልንጀራ›› ሰዎችን ሁሉ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከሰዎች ጋር ሰላም ከሚናገሩ››

በልባቸው ተንኰል እያለ

‹‹ልብ›› የሰውን አእምሮና ሐሳብ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ግን ስለ እነርሱ ክፉ ከሚያስቡ››

እንደ ተግባራቸው ስጣቸው… እንደ ክፋታቸው መጠን ክፈላቸው

ሁለቱም ሐረጐች ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ በአንድነት የተነገሩት እግዚአብሔር ሊቀጣቸው እንደሚገባ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡

እንደ እጃቸው ሥራ

‹‹እጅ›› ሰው የሚያደርገውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንዳደረጉት ነገር››

አጸፋውን መልስላቸው

‹‹የሚገባቸውን ሰጣቸው››

አልተረዱምና… አይገነባቸውም

ይህም ማለት፣ 1) እግዚአብሔር ክፉዎች ላይ ስለሚያደርገው ነገር ዳዊት እርግጠኛ ነው ወይም 2) ዳዊት እግዚአብሔር ክፉዎችን እንዲያጠፋ እየለመነ ነው፡፡

የያህዌን ሥራ አልተረዱምና

‹‹አልተረዱምና›› ሲል ችላ ብለዋል ወይም የያህዌን ሥራ ማክበር አልፈለጉም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ያደረገውን በክብር አላዩምና››

የእጆቹን ሥራ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እጆች›› ያህዌ ያደረገውን ወይም የፈጠረውን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ የፈጠረውን››

ያፈርሳቸዋል፤ መልሶም አይገነባቸውም

የክፉ ሰዎች መቀጣት እነርሱ እግዚአብሔር የሚያፈርሰው ሕንፃ ወይም ከተማ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡