am_tn/psa/027/011.md

1.4 KiB

መንገድህን አስተምረኝ

የሰው አኗኗር የሚሄድበት መንገድ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንድኖር የምትፈልገውን አስተምረኝ›› ወይም፣ ‹‹እንዳደርግ የምትፈልገውን አስተምረኝ››

በደልዳላ መንገድ ምራኝ

ያህዌ ጸሐፊውን ከጠላቶቹ መጠበቁ መሰናከል ወይም መውደቅ በማይችልበት መንገድ እርሱን መምራት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠብቀኝ››

ለጠላቶቼ ፍላጐት አሳልፈህ አትስጠኝ

ፍላጐት የሚለውን የነገር ስም ግሥ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶቼ የሚፈልጉትን እንዲያደርጉብኝ አሳልፈህ አትስጠኝ››

ተነሥተውብኛል

እዚህ ላይ ‹‹መነሣት›› ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን፣ ከሳሾች ክስ ለማቅረብ ፍርድ ቤት ውስጥ ቆመዋል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ላይ ክፉ ለመናገር ቆመዋል››

ዐመፅን ይረጫሉ

ዐመፅ የሚረጭ ነገር እንደሆነ እዚህ ላይ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ላይ ክፉ ነገር እንደሚያደርጉ ይናገራሉ››