am_tn/psa/027/009.md

1.7 KiB

ፊትህን ከእኔ አትሰውር

እዚህ ላይ፣ ‹‹ፊት›› የያህዌን ትኩረት ይወክላል፤ ፊትን መሰወር ችላ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ችላ አትበለኝ›› ወይም፣ ‹‹ለእኔ ማሰብህን አትተው››

ተቆጥተህ ከባርያህ ዘወር አትበል

ዳዊት ትሕትናውን ለማሳየት ራሱን፣ ‹‹ባርያህ›› ይላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አትቆጣኝ››

አትጣለኝ፤ አትተወኝ

‹‹መጣል›› እና፣ ‹‹መተው›› ሁለቱም ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ጸሐፊው እግዚአብሔር እንዲተወው እንደማይፈልግ አጥብቆ ይናገራል፡፡

ወይም አትተወኝ

‹‹እኔን›› የሚለው ውስጠ ታዋቂ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔን አትተወኝ›› ወይም፣ ‹‹እኔን አትጣለኝ››

የመዳኔ አምላክ

‹‹መዳኔ›› የሚለውን፣ ‹‹የምታድነኝ›› ማለት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የምታድነኝ አምላክ›› ወይም፣ ‹‹የምታድነኝ አንተ ስለሆንህ››

አባትና እናቴ ቢተውኝ እንኳ

‹‹አባትና እናቴ የሚተውኝ ቢሆን እንኳ››፤ እንዲህ አድርገዋል ወይም ያደርጋሉ ማለቱ አይደለም፡፡ ዋናው ነጥብ ያንን ቢያደርጉ እንኳ እግዚአብሔር እንደማይተወው መናገሩ ነው፡፡

ያህዌ ይቀበለኛል

‹‹ያህዌ ይጠብቀኛል›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ ይጠነቀቅልኛል››