am_tn/psa/027/007.md

1.5 KiB

ያህዌ፣ ድምፄን ስማ

‹‹ድምፅ›› የሚናገር ወይም የሚጣራ ሰውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ሰማኝ››

መልስልኝ

ይህ የሚያመለክተው ያህዌ የጸሐፊውን ጸሎት እንደሚሰማና የለመነውን እንደሚያደርግለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጸሎቴን መልስ›› ወይም፣ ‹‹የለመንሁህን አድርግልኝ››

ልቤ ይላል

‹‹ልብ›› የሰውን አእምሮና ሐሳብ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በልቤ አልሁ›› ወይም፣ ‹‹ለራሴ አልሁ››

ፊቱን ፈለግሁ

ወደ ያህዌ ለመጸለይ ወደ ቤተ መቅደስ የሚሄድ ሰው ያህዌን ለመፈለግ እንደሚሄድ ሰው እንደሆነ ተነግሯል፡፡ እዚህ ላይ፣ ‹‹ፊት›› የእግዚአብሔርን ሁለንተና ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለጸሎት ወደ ቤተ መቅደስህ እመጣለሁ››

ያህዌ ሆይ ፊትህን እሻለሁ

ወደ ያህዌ ለመጸለይ ወደ ቤተ መቅደስ የሚሄድ ሰው ያህዌን እንደሚፈልግ ተነግሯል፡፡ እዚህ ላይ ‹‹ፊት›› የእግዚአብሔርን ሁለንታ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወደ አንተ ለመጸለይ ወደ ቤተ መቅደስህ እመጣለሁ››