am_tn/psa/027/005.md

1.2 KiB

በመከራ ቀን

‹‹በመከራ ጊዜ›› ወይም፣ ‹‹መከራ ሲደርስብኝ››

እንዲሰውረኝ

‹‹እንዲደብቀኝ››

መሸሸጊያው… ድንኳኑ

ሁለቱም የሚያመለክቱት ጸሐፊው እግዚአብሔርን የሚያመልክበትን መገናኛ ድንኳን ነው፡፡

በድንኳኑ መሸፈኛ

‹‹መሸፈኛ›› የሚለው ቃል የሚያመለክተው መደበቂያና መሸሸጊያ ቦታ ነው፡፡

በዐለት ላይ ያነሣኛል

እግዚአብሔር ጸሐፊውን ከጠላቶቹ ማዳኑ ጠላቶቹ የማይደርሱበት ከፍ ያለ ዐለት ላይ እንዳደረገው መሆኑ ተነግሯል፡፡

ራሴ ከጠላቶቼ በላይ ከፍ ይላል

ይህ የሚያመለክተው ጠላቶቹን ሲያሸንፍ ጸሐፊው ያገኘውን ኩራት ወይም ክብር ነው፡፡ በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶቼን ሳሸንፍ ሰዎች ያከብሩኛል›› ወይም፣ ‹‹ጠላቶቼን እንዳሸንፍ በማድረግ እግዚአብሔር ያከብረኛል፡፡››