am_tn/psa/027/002.md

1.4 KiB

ሥጋዬን ለመብላት

አንድን ሰው ጨርሶ ማጥፋት የእርሱን ሥጋ መብላት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ቃል በቃል ሥጋውን ይበላሉ ማለት አይደለም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሊያጠፉኝ››

ባለጋራዎቼና ጠላቶቼ

ሁለቱም ቃሎች ተመሳሳይ ናቸው፡፡ እነዚህ ወደ እርሱ የቀረቡ ክፉ አድራጊዎች ናቸው፡፡

ተሰናክለው ወደቁ

ይህ የሚያመለክተው የጸሐፊው ጠላቶች እርሱን የማጥፋት ዕቅዳቸው አለመሳካቱን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አልተሳካላቸውም›› ወይም፣ ‹‹ፈረሰባቸው››

ሰራዊት ቢሰፍርብኝ እንኳ

‹‹ሰራዊት ቢከበኝ እንኳ›› ወይም ‹‹ሰራዊት ድንኳኑን በዙሪያየ ቢያደርግ እንኳ››

ልቤ አይፈራም

‹‹ልብ›› መላውን ሰው ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አልፈራም››

ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ

የጸሐፊው ጠላቶች ራሳቸው ጦርነት እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶቼ ሊወጉኝ ቢመጡ እንኳ››

ልበ ሙሉ ነኝ

‹‹እግዚአብሔር እንደሚረዳኝ እተማመናለሁ››