am_tn/psa/027/001.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ተጓዳኝ ሐሳብ በዕብራይስጥ ቅኔ የተለመደ ነው፡፡

የዳዊት መዝሙር

ይህም ማለት፣ 1) መዝሙሩን የጻፈ ዳዊት ነው ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) መዝሙሩ በዳዊት አዘማመር ስልት ነው፡፡

ያህዌ ብርሃኔ ነው

እዚህ ላይ ‹‹ብርሃን›› ሕይወትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ የሕይወቴ ምንጭ ነው››

ማንን እፈራለሁ?

ጥያቄው ዳዊት የሚፈራው አለመኖሩን አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማንንም አልፈራም››

ያህዌ የሕይወቴ መጠጊያ ነው

ይህ ያህዌ ሰዎች የሚጠጉበት ቦታ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሰላም እንድኖር የሚጠብቀኝ ያህዌ ነው››

የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?

ጥያቄው ዳዊትን የሚያስደነግጠው ነገር አለመኖሩን አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሚያስደነግጠኝ የለም››