am_tn/psa/026/001.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ተጓዳኝ ሐሳብ በዕብራይስጥ ቅኔ የተለመደ ነው፡፡

የዳዊት መዝሙር

ይህም ማለት፣ 1) መዝሙሩን የጻፈ ዳዊት ነው ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) መዝሙሩ በዳዊት አዘማመር ስልት ነው፡፡

ተመላለስሁ

‹‹መመላለስ›› አኗኗርን የሚያመለክት ምሳሌ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ኖርሁ››

በያህዌ

‹‹ያህዌን›› በተመለከተ በሦስተኛ ሰው ደረጃ የተነገረውን በሁለተኛ ሰው ደረጃ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በአንተ››

ያለ መናወጥ

መጠራጠር ሚዛን መሳትና ወዲያ ወዲህ ማለት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያለ መጠራጠር››

ፈትነኝ

‹‹መርምረኝ››

ልቤንና የውስጤን ንጽሕና መርምር

እዚህ ላይ፣ ‹‹የውስጤ›› እና፣ ‹‹ልቤ›› ዝንባሌን ያመለክታሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዝንባሌዬ መልካም መሆን አለመሆኑን መርምር››

ኪዳናዊ ታማኝነትህ በዐይኔ ፊት ነውና

እዚህ ላይ፣ ‹‹ዐይን›› የሰውን ሐሳብና አንድን ነገር ዐይን ፊት ማድረግ ስለዚያ ነገር መገንዘብን ያመለክታል፡፡ ‹‹ታማኝነት›› የተሰኘውን የነገር ስም እንደ ቅጽል መተጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ሁልጊዜም ኪዳናዊ ታማኝነትህን እገነዘባለሁ›› ወይም፣ ‹‹አንተ ለኪዳንህ ታማኝ መሆንህን ሁሌም እገነዘባለሁ››

በታማኝነትህ ተመላለስሁ

‹‹መመላለስ›› አኗኗርን ይወክላል፡፡ ‹‹ታማኝነት›› የተሰኘውን የነገር ስም እንደ ቅጽል መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሕይወቴን እንደ አንተ ታማኝነት እኖራለሁ›› ወይም፣ ‹‹አሁን እንደምኖረው የምኖረው አንተ ታማኝ ስለሆንህ ነው››