am_tn/psa/025/020.md

979 B

አታሳፍረኝ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶቼ እንዲያሳፍሩኝ አትተዋቸው››

ወደ አንተ እጠጋለሁ!

ለጥበቃ ወደ ያህዌ መሄድ ወደ እርሱ መጠጋት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጥበቃ እንድታደርግልኝ ወደ አንተ እጠጋለሁ››

ታማኝነትና ቅንነት ይጠብቁኝ

‹‹ታማኝነት›› እና፣ ‹‹ቅንነት›› እንደ ሰው የሚጠብቁ ነገሮች እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ እነዚህን የነገር ስሞች ቅጽል ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ታማኝ መሆኔና ቅን የሆነውን ነገር ማድረጌ ይጠብቁኝ›› ወይም፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ ታማኝና ቅን ስለሆንሁ ጠብቀኝ››

ጠብቀኝ

‹‹አድነኝ››