am_tn/psa/025/014.md

1.1 KiB

የያህዌ ወዳጆች

‹‹ያህዌ… ወዳጅ ነው›› አንዳንዶች፣ ‹‹ያህዌ ምስጢሩን›› በማለት ተርጉመውታል፡፡ ምስጢሩን ለእነርሱ መናገሩ ምን ያህል የጠበቀ ወዳጃቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡

ዐይኖቼ ዘወትር ያህዌ ላይ ናቸው

‹‹ዐይኖች›› ማየትን ይወክላሉ፡፡ እንዲረዳው ያህዌን እንደሚያይ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንዲረዳኝ ሁሌም ያህዌን እመለከታለሁ›› ወይም ‹‹እንዲረዳኝ ሁሌም በያህዌ እታመናለሁ››

እግሮቼን ከመረብ ነጻ ያደርጋልና

መረብ ወጥመድ ነው፡፡ አደጋ ላይ ያሉ ሰዎች እግሮቻቸው በመረብ እንደ ተጠላለፉ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከአደጋ ያወጣኛል››

ወደ እኔ ተመለስ

ያህዌ ትኩረቱን ሰው ላይ ማድረጉ ወደ እርሱ መመለስ እንደሆነ ተነግሯል፡፡