am_tn/psa/025/001.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ተጓዳኝ ሐሳብ በዕብራይስጥ ቅኔ የተለመደ ነው፡፡

ሕይወቴን አነሣለሁ

‹‹ሕይወቴን አነሣለሁ›› ምሳሌያዊ አባባል ነው፡፡ ይህም ማለት፣ 1) ጸሐፊው ራሱን ለያህዌ እየሰጠ ነው፤ ማለት ሙሉ በሙሉ በያህዌ ይታመናል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ራሴን ለአንተ እሰጣለሁ›› ወይም 2) የምስጋና ጸሎት ለያህዌ ማቅረቡ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አመልክሃለሁ፤ ከፍ አደርግሃለሁ››

አታሳፍረኝ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶቼ እንዲያሳፍሩኝ አትተዋቸው››

በድል አድራጊነት በእኔ ላይ ደስ አይበላቸው

‹‹እኔን በማሸነፍ ደስ አይበላቸው›› - ‹‹በእኔ ላይ›› የሚለው ሐረግ ጠላቶቹ እንዳሸነፉትና በድል እንደ ቆሙ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔን በማሸነፍ ደስ አይበላቸው››

አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም

‹‹አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አይፈሩ›› በጠላት መሸነፍ እፍረት ያመጣል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተን ተስፋ የሚያደርጉን ጠላት አያሸንፋቸው››

አንተን ተስፋ የሚያደርጉ

‹‹የሚታመኑብህ››

ከሐዲዎች የሆኑ

‹‹አታላዮች›› ወይም፣ ‹‹የሚያጭበረብሩ››

ያለ ምክንያት

‹‹ምንም ምክንያት ሳይኖር››