am_tn/psa/023/005.md

1.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እግዚአብሔር በቤቱ እንግድነት ተቀብሎ እንደሚጠብቀው ሰው እንደሆነ ጸሐፊው ይናገራል፡፡

ገበታ አዘጋጀህልኝ

ገበታ ግብዣን ያመለክታል፤ ሰዎች ምግቦችን ሁሉ ገበታው ላይ ይኖራሉ፡፡

በጠላቶቼ ፊት

የዚህ ትርጒም ጸሐፊው እርሱ የተከበረ የጌታ እንግዳ እንደሆነና እርሱም ከአደጋ ስለሚጠብቀው እንደማይሰጋ ጸሐፊው ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ጠላቶቼ እያዩ››

ራሴን በዘይት ቀባህ

ሰዎች ለእንግዳው ክብር ራሱን በዘይት ይቀቡት ነበር፡፡

ጽዋዬም ሞልቶ ይፈስሳል

ወይን ሞልቶ የሚፈስስ ጽዋ ብዙ በረከትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሞልቶ እስኪፈስ ድረስ ጽዋዬን ሞላኸው›› ወይም፣ ‹‹ብዙ በረከት ሰጠኸኝ››