am_tn/psa/023/003.md

956 B

አጠቃላይ መረጃ

ይህ መዝሙር እረኛ ለበጐቹ እንደሚያስብ እግዚአብሔርም ለእኛ እንደሚያስብ መናገር ቀጥሏል፡፡

ነፍሴን መለሳት

ይህ ማለት ደካማውን ሰው እግዚአብሔር ብሩቱ ያደርገዋል ያሳርፈዋል ማለት ነው፡፡

በትክክለኛው መንገድ መራኝ

እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕይወት መኖርን ለአንድ ሰው ማሳየት በጉን በትክክለኛ መንገድ እንደሚመራ እረኛ መሆን እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በትክክል መኖርን ያሳየኛል››

ስለ ስሙ ሲል

‹‹ስለ ስሙ›› የሚለው ሐረግ የእርሱን ማንነት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለ ማንነቱ›› ወይም፣ ‹‹ሰዎች እንዲያከብሩት››