am_tn/psa/022/028.md

1.5 KiB

መንግሥት የያህዌ ነው

‹‹መንግሥት የሚገባው ለያህዌ ነው›› እዚህ ላይ፣ ‹‹መንግሥት›› የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን እንደ ንጉሥ መግዛት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ንጉሥ ነውና››

ሕዝቦችንም የሚገዛ እርሱ ነው

‹‹ሕዝቦች›› የሚያመለክተው ሰዎችን ሁሉ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በየአገሩ ያሉ ሰዎች››

ይበላሉ

ሰዎቹ በአንድነት በደስታ ይበላሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አብረው ይበላሉ›› ወይም፣ ‹‹የደስታ ምግብ አብረው ይበላሉ››

ወደ ዐፈር የሚወርዱ ሁሉ… ራሳቸውን ማዳን የማይችሉ

ሁለቱም ሐረጐች የሚያመለክቱት ስለ አንድ ወገን ነው፡፡ ሰዎች ሁሉ ሟች ስለ ሆኑ ሁለቱም የሚናገሩት ስለ ሰዎች ሁሉ ነው፡፡

ወደ ዐፈር የሚወርዱ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ዐፈር›› የሚያመለክተው መቃብርን ነው፡፡ ‹‹ወደ ዐፈር የሚወርዱ›› የሚለው የሚያመለክተው የሚሞቱ ሰዎችን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እየሞቱ ያሉ›› ወይም፣ ‹‹የሚሞቱ››

ራሳቸውን ማዳን የማይችሉ

‹‹ሕይወታቸውን ማዳን የማይችሉ›› ወይም፣ ‹‹ራሳቸውን ከሞት የማያድኑ››