am_tn/psa/022/026.md

1.9 KiB

ችግረኞች ይበላሉ ይጠግባሉ

ይህ የሚያመለክተው ጸሐፊው ቃል የገባውን መሥዋዕት ካቀረበ በኃላ የሚኖረውን የኅብረት ምግብ ነው፡፡ እርሱ ለመሥዋዕት ያቀረበውን እንስሳ ክፍል እንዲበሉ ችግረኞችን ይጋብዛል፡፡

ያህዌን የሚፈልጉት

ያህዌን ማወቅና እርሱን ደስ ማሰኘት የሚፈልጉ እርሱን ራሱን ለማግኘት እንደሚፈልጉ ተነግሯል፡፡

ልባችሁ ለዘላለም ሕያው ይሁን

እዚህ ላይ፣ ‹‹ልብ›› የሰውን ሁለንተና ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለዘላለም ሕያው ሁኑ››

ልባችሁ ለዘላለም

እዚህ ላይ፣ ‹‹የእናንተ›› የሚለው ችግረኞቹን ነው፡፡

ያስታውሳሉ ወደ ያህዌ ይመለሳሉ

ለያህዌ መታዘዝ የሰዎች ወደ ያህዌ መመለስ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌን ያስታውሱታል ይታዘዙለታል››

የሕዝቦች ወገኖች ሁሉ በፊትህ ወድቀው ይሰግዳሉ

ይህ ከመጀመሪያው ዐረፍተ ነገር ክፍል ጋር ተመሳሳይ ነገር ነው የሚናገረው፡፡ ጸሐፊው በየቦታው ያሉ ሰዎች ሁሉ ያህዌን እንደሚያመልኩና እንደሚታዘዙለት አጽንዖት ይሰጣል፡፡

በፊትህ ወድቀው ይሰግዳሉ

ይህ የሚያመለክተው ክብርንና ምስጋናን መስጠትን ነው፡፡

በፊትህ

እዚህ ላይ፣ ‹‹አንተ›› የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡ ከመጀመሪያው ዐረፍተ ነገር ክፍል ጋር እንዲጣጣም በሦስተኛ ሰው ደረጃ መተርጐም አለበት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በፊቱ››