am_tn/psa/022/024.md

2.4 KiB

የተጨነቀውን ሰው ጭንቀት አልናቀም፤ ቸልም አላለምና

ይህም ማለት፣ 1) መከራ ላይ ስለሆነ የተጨነቀውን ሰው አልናቀም ወይም 2) የተጨነቀውን ሰው መከራ አቅልሎ አላየም ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

አልናቀም ወይም አልተጸየፈም

በመሠረቱ ሁለቱም ተመሳሳይ ናቸው፤ የተጨነቀውንና በመከራ ያለውን እግዚአብሔር አለመርሳቱን አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡

አልናቀም

አጥብቆ አልጠላም

የተጨነቀውን ሰው መከራ… አልተጸየፈም

እዚህ ላይ፣ መከራ የሚያመለክተው ሰውየውን ነው፡፡ አንድን ነገር መጸየፍ አጥብቆ መጥላት ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የተጨነቀውን ሰው መከራ አጥብቆ አልጠላም››

የተጨነቀው ሰው መከራ… ከእርሱ… የተጨነቀው ጮኸ

ይህም ማለት፣ 1) ጸሐፊው እግዚአብሔር መከራ ውስጥ ያሉትን እንዴት እንደሚያይ እየተናገረ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መከራ ውስጥ ያሉት… ከእነርሱ… መከራ ውስጥ ያሉት ጮኹ›› ወይም 2) ጸሐፊው በተለይ እርሱን እንዴት እንደሚያይ እየተናገረ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከመከራዬ የደረሰብኝ ጭንቀት… ከእኔ… ጮኽሁ››

ፊቱን ከእርሱ አልሰወረም

ከሰው ፊትን መሰወር እርሱን ችላ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ትኩረቱን ከእርሱ አላነሣም›› ወይም፣ ‹‹ችላ አላለውም››

ሰማ

‹‹አደመጠ›› ጩኸታቸውን ሲሰማ ምላሽ መስጠቱ ግልጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መለሰ›› ወይም፣ ‹‹ረዳ››

በአንተ

‹‹አንተ›› የሚለው ያህዌን ነው፡፡

ስዕለቴን እፈጽማለሁ

ይህ የሚያመለክተው ጸሐፊው ለእግዚአብሔር እንደሚያቀርብ ቃል የገባውን ነው፡፡

እርሱን በሚፈሩት ፊት

‹‹እርሱ›› የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡ ‹‹አንተ›› ሊባልም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተን በሚፈሩ ፊት››