am_tn/psa/022/020.md

1.3 KiB

ነፍሴን ታደጋት

‹‹ነፍስ›› የሰውን ሁለንተና ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ታደገኝ››

ከሰይፍ

ሰይፍ ለአደገኛ ጠላት የሚሰጥ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሊገድሉኝ የሚፈልጉ›› ወይም፣ ‹‹ጠላቶቼ››

ውድ ሕይወቴን

‹‹የከበረች ሕይወቴን›› ወይም፣ ‹‹ያለችኝን ብቸኛ ሕይወቴን››

ከዱር ውሾች ጥፍር… ከአንበሶች አፍ… ከዱር በሬዎች ቀንድ

ጸሐፊው ጠላቶቹ ምን ያህል አደገኞች መሆናቸውን አጽንዖት ለመስጠት የዱር ውሾች፣ አንበሶችና የዱር በሬዎች እንደሆኑ ይናገራል፡፡ በተጨማሪም ጥፍር፣ አፍና ቀንድ በምሳሌያዊ አነጋገር እንስሳትን ሁሉ ያመለክታል፡፡ ጸሐፊው ለእነዚህ ነገሮች አጽንዖት የሰጠው እንስሶች ሌላውን ለመግደል የሚጠቀሙት በእነዚህ ነገሮች በመሆኑ ነው፡፡

የዱር ውሾች… የዱር በሬዎች

እዚህ ላይ ‹‹ዱር›› የሚለው ቃል እንስሶቹን ማንም ይዞአቸው ወይም አልምዶአቸው፡፡ እንደማያውቅ ለማመልከት ነው፡፡