am_tn/psa/022/016.md

1.6 KiB

ውሾች ከበቡኝ

ጸሐፊው ጠላቶቹ እንደ ውሾች እንደሆኑ ይናገራል፡፡ ጠላቶቹ የሞተ እንስሳ እንደሚበሉ የዱር ውሾች ወደ እርሱ እየቀረቡ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶቼ እንደ ውሾች ከበቡኝ››

የክፉዎች ሸንጐ

‹‹የክፉዎች ጉባኤ›› ወይም፣ ‹‹የክፉዎች ቡድን››

በዙሪያዬ

ክብ ሠርተው ቆሙ

እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩ

ይህም ስለ ውሾቹ ነው የሚናገረው ጸሐፊው ጠላቶቹ እንደሚናከሱና በጥርሳቸው እጆችና እግሮቹን እንደ ቸነከሩ ይናገራል፡፡

ቸነከሩኝ

ስል በሆነ ነገር ወጉኝ

ዐጥንቶቼን መቁጠር እችላለሁ

ይህም ማለት፣ 1) ጸሐፊው በጣም ከሲታ ስለ ነበር ዐጥንቶቹን ማየት ይችላል ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዐጥንቶቼን ሁሉ ማየት እችላለሁ›› ወይም፣ ‹‹ዐጥንቶቼን መንካት እችላለሁ›› ወይም 2) ይህ የሚናገረው ስለ ውሾቹ ሲሆን፣ ሥጋውን ከገነጣጠሉ በኃላ ዐጥንቶቼን ማየት ቻሉ ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

አፍጥጠው ያዩኛል፤ ይመለከቱኛል

‹‹ያዩኛል›› እና፣ ‹‹ይመለከቱኛል›› በመሠረቱ አንድ ቢሆኑም፣ ሰዎች በፍርሃት እንደሚያዩትና እንደሚቀልዱበት አጽንዖት ይሰጣል፡፡