am_tn/psa/022/014.md

2.3 KiB

እንደ ውሃ ፈሰስሁ

ይህን በሌለ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ውሃ የፈሰሰሁ መሰለኝ››

እንደ ውሃ ፈሰስሁ

ከእንስራ ወደ ውጭ እንደ ፈሰሰ ውሃ ያበቃለትና ፍጹም ደካማነት እንደ ተሰማው ጸሐፊው ይናገራል፡፡

ዐጥንቶቼ ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ

‹‹ዐጥንቶቼ ሁሉ ተናጉ›› ጸሐፊው አንድ ዐይነት የአካል ሕመም ደርሶበት ይሆናል፡፡ ወይም ስሜታዊውን ሕመም እንደ አካላዊ ሕመም እያመለከተ ይሆናል፡፡

ልቤ እንደ ሰም… ውስጤ

ልቡ እንደ ሰም እንደ ቀለጠ ሰው፣ ጸሐፊው ከእንግዲህ ምንም ወኔ እንደሌለው ይናገራል፡፡ እዚህ ላይ፣ ‹‹ልብ›› የሚያመለክተው፣ ‹‹ወኔን›› ነው፡፡

ሰም

በአንጻራዊ በጣም ዝቅ ባለ ሙቀት እንኳ የሚቀልጥ ነገር

በውስጤ

‹‹እኔ ውስጥ››

ብርታቴ እንደ ገል ደረቀ

ጸሐፊው በቀላሉ እንደሚሰበር የደረቀ ሸክላ ስባሪ ዐቅመ ቢስነት እንደ ተሰማው ይናገራል፡፡

የሸክላ ስባሪ

እቤት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል ከሸክላ የተሠራ ነገር

ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ተጣበቀ

‹‹ምላሴ ከትናጋዬ ጋር ተጣበቀ›› ምናልባትም ጸሐፊው በጣም ጠምቶት እንደ ነበር እየተናገረ ይሆናል፡፡ ወይም መድከሙ የመድረቅ ያህል እንደሆነበት እየተናገረ ይሆናል፡፡

በሞት ዐፈር አጋደምኸኝ

‹‹የሞት ዐፈር›› ማለት 1) ከሞተ በኃላ ወደ ዐፈር የተለወጠ ሰው ማለት ይሆናል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንድሞትና ዐፈር እንድሆን አደረግኸኝ›› ወይም 2) ስለ መቃብርና በዚያም አማካይነት እግዚአብሔር ጸሐፊው እንዲሞት እንዳደረገ መናገሩ ይሆናል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በመቃብሬ አጋደምኸኝ››

አጋደምኸኝ

‹‹አንተ›› የሚለው የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው፡፡