am_tn/psa/022/011.md

1.6 KiB

ከእኔ አትራቅ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወደ እኔ ቅረብ››

መከራ እየተቃረበ ነውና

ጸሐፊው፣ ‹‹መከራ ወደ እርሱ እየቀረበ ያለ ነገር እንደሆነ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶቼ ወደ እኔ እየቀረቡ ነውና››

የሚረዳ የለም

‹‹ረዳት የለም››

ብዙ ኮርማዎች ከበቡኝ፣ ኀይለኛ የባሳን በሬዎችም በዙሪያየ ቆሙ

ጸሐፊው ጠላቶቹ እንደ ኮርማ እንደሆኑ ይናገራል፡፡ ይህ የሚያሳየው ጠላቶቹ ምን ያህል አደገኛና ብርቱ መሆናቸውን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ኮርማዎች የከበቡኝ ብዙ ጠላቶች አሉኝ እነርሱ ዙሪያዬን እንደ ቆሙ ኀይለኛ የባሳን በሬዎች ናቸው››

አፋቸውን አስፍተው ከፈቱብኝ

ጸሐፊው ጠላቶቹ እርሱን ለመብላት አፋቸውን እንደ ከፈቱ አንበሶች እንደሆኑ ይናገራል፡፡ ጠላቶቹ እርሱን ለማዋረድ ሐሰት እየተናገሩ ይሆናል፡፡ ወይም እንደሚያጠቁት እየዛቱበት ይሆናል፡፡

እንደሚነጥቅና እንደሚያገሣ አንበሳ

ጸሐፊው ጠላቶቹ እንደ አንበሳ እንደሆኑ ይናገራል፡፡ ይህም ጠላቶቹ ምን ያህል ኀይለኞችና አደገኞች መሆናቸውን አጽንዖት ይሰጣል፡፡