am_tn/psa/022/009.md

1.3 KiB

አንተ ግን

ጸሐፊው፣ ‹‹ግን›› በሚል ቃል የተጠቀመው ለምን እርሱን ለመርዳት እንደማይመጣ ግራ መጋባቱን ለማሳየትና እግዚአብሔር ለመጠየቅ ነው፡፡

ከማሕፀን አወጣኸኝ

ይህ ‹‹እንድወለድ አደረግህ›› ማለት ነው፡፡

በእናቴ ጡት ሳለሁ

ይህ ማለት ገና ሕፃን እያለ በያህዌ ይተማመን ነበር ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእናቴ ጡት እጠባ በነበረበት ጊዜ እንኳ››

ከእናቴ ማሕፃን ስወጣም በአንተ ተጣልሁ

‹‹ተጣልሁ›› የሚለው ቃል ያህዌ እንደራሱ ልጅ ተቀብሎ ተጠነቀቀለት ለማለት ጥቅም ላይ የዋለ ቃል ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ተወለድሁ አንተ ተቀበልኸኝ››

አንተ አምላኬ ነህ

ይህ የሚያመለክተው ያህዌ ዘወትር ለጸሐፊው ይጠነቀቅለት እንደ ነበር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ተጠነቀቅህልኝ››

በእናቴ ማሕፀን ሳለሁ

‹‹ከመወለዴ በፊት››