am_tn/psa/022/006.md

1.6 KiB

እኔ ትል ነኝ፤ ሰው አይደለሁም

ጸሐፊው እርሱ ትል እንደሆነ ይናገራል፡፡ ይህም እርሱ ከንቱ እንደሆነ ወይም ሰዎች እንደ ከንቱ ነገር እንደሚቆጥሩት አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ እንደ ትል ነኝ እንጂ፣ ሰው አይደለሁም››

ሰው ያላገጠብኝ፤ ሕዝብም የናቀኝ ነኝ

ሁለቱም ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ‹‹ሕዝብም የናቀኝ›› የሚለውን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች ሁሉ ዋጋ እንደሌለኝ በመቁጠር ይጠሉኛል››

ያላግጡብኛል፤ ይሣለቁብኛል፤ ራሳቸውንም ይነቀንቁብኛል

እነዚህ ሦስት ሐረጐች ተመሳሳይ ትርጒም አላቸው፤ ሰዎች ምን ያህል እንዳዋረዱት አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡

ራሳቸውንም ይነቀንቁብኛል

ይህ ሰውን የመናቅ ምልክት ነው፡፡

በያህዌ ተማምኖአል… በእርሱ ደስ የተሰኘበትን

ሰዎች እንዲህ ያሉት በጸሐፊው ለማፌዝ ነው፡፡ ያህዌ እንደሚታደገው በእርግጥ አያምኑም፡፡

እስቲ ይታደገው

‹‹እስቲ ያህዌ ይታደገው››

በእርሱ ደስ የተሰኘበትን

ይህም ማለት፣ 1) ‹‹ያህዌ በእርሱ ደስ ተሰኝቶአልና›› ወይም 2) ‹‹እርሱ በያህዌ ደስ ተሰኝቶአልና››