am_tn/psa/022/001.md

2.6 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ መረጃ

ተጓዳኝ ሐሳብ በዕብራይስጥ ቅኔ የተለመደ ነው፡፡

ለመዘምራን አለቃ

‹‹ይህ የመዘምራን መሪ በአምልኮ ጊዜ የሚጠቀምበት ነው››

የንጋት አጋዘን

ይህ የሚያመለክተው የዜማውን ስልት ሊሆን ይችላል፡፡

የዳዊት መዝሙር

ይህም ማለት፣ 1) መዝሙሩን የጻፈው ዳዊት ነው ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) መዝሙሩ በዳዊት አዘማመር ስልት ነው ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

አምላኬ፣ አምላኬ

ጸሐፊው፣ ‹‹አምላኬ›› የሚለውን የደገመው እግዚአብሔር እንዲሰማው አጥብቆ መፈለጉን አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡

አምላኬ ለምን ተውኸኝ?

ጸሐፊው ጥያቄውን ያነሣው እግዚአብሔር እንደ ተወው ስለ ተሰማው ነው፡፡ ይህን ጥያቄ እንደሆነ መተው ይሻላል፡፡ እንደ ዐረፍተ ነገር መተርጐምም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አምላኬ ሆይ፣ አንተ እንደ ተውኸኝ ይሰማኛል!

ተውኸኝ

‹‹ብቻዬን ተውኸኝ››

እኔን ከማዳን፣ ከመቃተቴ ቃል ለምን ራቅህ?

ጸሐፊው ጥያቄውን ያነሣው እግዚአብሔር ከእርሱ በጣም እንደ ራቀ ስለ ተሰማው ነው፡፡ ይህን ጥያቄ እንደሆነ መተው ይሻላል፡፡ በዐረፍተ ነገር መተርጐምም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ እኔን ከማዳንና ከመቃተቴ ቃል ርቀሃል››

ከመቃተቴ ቃል ርቀሃል

እግዚአብሔር እንዳልሰማው ጸሐፊው የነበረው ስሜት እግዚአብሔር ከመቃተቱ ቃል በጣም የራቀ ያህል መሆኑን ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለሚሰማኝ ጭንቀት ስናገር የማትሰማኝ ለምንድነው? ወይም ‹‹ስለ መከራዬ ነገርሁህ አንተ ግን ወደ እኔ አልመጣህም››

በቀን… በሌሊት

ጸሐፊው፣ ‹‹ቀን›› እና፣ ‹‹ሌሊት›› በተሰኙ ቃሎች የተጠቀመው ዘወትር ወደ እግዚአብሔር እንደሚጸልይ ለማመልከት ነው፡፡

ዝም አላልሁም

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አሁንም እየተናገርሁ ነው››