am_tn/psa/020/007.md

1.3 KiB

አንዳንዶች በሰረገላ ሌሎች በፈረስ ይታመናሉ

‹‹ሰረገላ›› እና፣ ‹‹ፈረስ›› የንጉሡን ሰራዊት ይወክላሉ፡፡

ሌሎች በፈረሶች

‹‹ይታመናሉ›› ውስጠ ታዋቂ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሌሎች በፈረስ ይታመናሉ››

እንጠራለን… እንነሣለን

‹‹እኛ›› የሚያመለክተው ጸሐፊውንና አንባቢዎቹን ነው፡፡

እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ

‹‹እነርሱ›› የሚያመለክተው በሰረገሎችና በፈረሶች የሚተማመኑትን ሰዎች ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እግዚአብሔር ያሰነካክላቸዋል፤ ይጥላቸዋል››

ተሰነካክለው ወደቁ

ሁለቱም ግሦች ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሁለቱም የሚያመለክቱት በጦርነት መሸነፍን ነው፡፡

እኛ ተነሣን ጸንተንም ቆምን

‹‹እኛ ተነሥተን ቀጥ ብለን እንቆማለን›› ሁለቱን ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሁለቱም የሚያመለክቱት በጦርነት ድል ማድረግን ነው፡፡