am_tn/psa/020/003.md

1.3 KiB

ያስብህ

‹‹ያስብህ›› የተባለው እግዚአብሔር ስለሚረሳ አይደለም፡፡ ያስታውስህ ወይም ያስብልህ ለማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ ያስታውስህ››

እርሱ

ይህ ቃል የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡

ሴላ

ይህ ቃል እንዴት እንደሚዘምሩ ወይም የሙዚቃ መሣሪያቸውን እንደሚጫወቱ ለሕዝብ የሚናገር የሙዚቃ አገላለጽ ነው፡፡ አንዳንድ ትርጒሞች የዕብራይስጡን ቃል ይጽፋሉ፤ አንዳንድ ትርጒሞች ያንን አያደርጉም፡፡ መዝሙር 3፥2 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

ይስጥህ

‹‹ይለግሥህ››

የልብህን መሻት

‹‹ልብ›› የሰውን ሁለንተና ይወክላል፡፡ ‹‹መሻት›› የሚለውን ስም ግሥ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የምትሻውን›› ወይም፣ ‹‹የምትፈልገውን››

ዕቅድህን ሁሉ ያሳካልህ

‹‹ዕቅድ›› የሚለውን የነገር ስም ግሥ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያቀድኸውን ሁሉ ለማሳካት ይርዳህ››