am_tn/psa/020/001.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህ መዝሙር የሚጀምረው ሰዎች ለእስራኤል ንጉሥ እየተናገሩ ነው፡፡

አጠቃላይ መረጃ

ተጓዳኝ ሐሳብ በዕብራይስጥ ቅኔ የተለመደ ነው፡፡

ለመዘምራን አለቃ

‹‹ይህ በአምልኮ ጊዜ ለመዘምራን መሪ የሚሆን ነው››

የዳዊት መዝሙር

ይህም ማለት 1) መዝሙሩን የጻፈ ዳዊት ነው፤ ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው፤ ወይም 3) መዝሙሩ በዳዊት አዘማመር ስልት ነው፡፡

ይረዳሃል

እዚህ ላይ፣ ‹‹አንተን›› የሚለው ንጉሡን ነው፡፡

በመከራ ቀን

‹‹በችግር ቀን›› ወይም፣ ‹‹ችግር ሲገጥምህ››

የያዕቆብ አምላክ ስም ይጠብቅህ

ይህም ማለት፣ 1) እዚህ ላይ፣ ‹‹ስም›› የያህዌን ኀይል ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የያዕቆብ አምላክ ኀይል ይጠብቅህ›› ወይም፣ ‹‹የያዕቆብ አምላክ በኃይሉ ይጠብቅህ›› ወይም 2) እዚህ ላይ፣ ‹‹ስም›› እግዚአብሔርን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የያዕቆብ አምላክ ይጠብቅህ››

ከመቅደሱ ረድኤት ይላክልህ

እግዚአብሔር በመቅደሱ ሆኖ መርዳቱ ርዳታ መላክ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ከመቅደሱ ረድኤት ይላክልህ››

መቅደሱ… ጽዮን

ሁለቱም ቃሎች የሚያመለክቱት በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው፡፡