am_tn/psa/019/013.md

1.7 KiB

ባርያህን ጠብቀው

ፈሊጣዊው አነጋገር ባርያው ማድረግ ከማይፈልገው ኀጢአት መራቅ እንደሚፈልግ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ባርያህን ከማድረግ ጠብቀው›› ወይም፣ ‹‹እንዳላደርግ ርዳኝ››

ባርያህ

አክብሮቱን ለማሳየት ለእግዚአብሔር ሲናገር ዳዊት ራሱን ባርያ በማለት ይጠራል፡፡ መዝሙር 19፥11 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

አይግዙኝ

ኀጢአት ሰውን የሚገዛ ንጉሥ እንደ ሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኀጢአቶቼ እንደ ንጉሥ አይግዙኝ››

ከብዙ መተላለፍ አንጻኝ

‹‹አንተ ላይ እንዳላምፅ አድነኝ›› ወይም፣ ‹‹ብዙ ኀጢአት ከማድረግ››

የአፌ ቃልና የልቤ ሐሳብ

እነዚህ ቃሎች በአንድነት ሲወሰዱ አንድ ሰው የሚናገረውና የሚያስበው ሁሉ ማለት ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የምናገረውና የማስበው ሁሉ››

በፊትህ የተወደደ ይሁን

‹‹በፊትህ ተቀባይነት ያለው›› ወይም ‹‹ደስ የሚያሰኝህ››

በፊትህ

ፊት ፍርድና ሚዛንን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በአንተ ፍርድ››

ያህዌ ዐለቴ

ጸሐፊው ያህዌ ከጠላቶቹ የሚሸሸግበት ዐለት እንደሆነ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ፣ አንተ ለእኔ እንደ ዐለት ነህ››