am_tn/psa/019/001.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ተጓዳኝ ሐሳብ በዕብራይስጥ ቅኔ የተለመደ ነው፡፡

ለመዘምራን አለቃ

‹‹ይህ በአምልኮ የመዘምራን መሪ የሚጠቀምበት ነው››

የዳዊት መዝሙር

ይህም ማለት፣ 1) መዝሙሩን የጻፈው ዳዊት ነው ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው፤ ወይም 3) መዝሙሩ በዳዊት አዘማመር ስልት መሠረት ነው፡፡

ሰማያት ይናገራሉ

ሰማያት እንደ ሰው እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰማያት ያሳያሉ›› ወይም፣ ‹‹ሰማያት ያውጃሉ››

የሰማያትም ጠፈር የእጁን ሥራ ያሳውቃሉ

ሰማያት አስተማሪ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰማያት የእግዚአብሔርን እጅ ሥራ ያስታውቁናል››

የእጁ ሥራ

‹‹ፍጥረቱ›› ወይም፣ ‹‹እርሱ የሠራው ዓለም››

ድምፃቸው ወጣ

የፍጥረት ውበት ፍጥረት የሚናገር ሰው እንደሆነ ያመለክታል፡፡ እነዚሁ ቃሎች በየቦታው ከሚፈስስ ውሃ ጋር ተመሳስለዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ፍጥረት ለሁሉም እንደሚናገር ሰው ነው››

ንግግር የለም፤ ቃል የለም፤ ድምፃቸውም አልተሰማም

እነዚህ ሐረጐች የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቁጥሮች ምሳሌያዊ አነጋገር መሆናቸውን በግልጽ ያመለክታሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ድምፅ ወይም ቃል የለም፤ በጆሮው ድምፅ የሰማ ሰው የለም››

ድምፃቸው አልተሰማም

ሌሎች ትርጒሞች፣ ‹‹ድምፃቸው ባልተሰማበት›› ይላሉ፤ ይህም የፍጥረት፣ ‹‹ድምፅ›› በየቦታው እንደሚሰማ አጽንዖት ይሰጣል፡፡