am_tn/psa/018/046.md

1.3 KiB

ዐለቴ ይመስገን

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ ዐለቴ ነው፤ መመስገን ይገባዋል›› ወይም፣ ‹‹ሕዝቦች ዐለቴን ያመስግኑት››

ዐለቴ

እዚህ ላይ ጸሐፊው ጠላቶቹ እንዳያገኙት ያህዌ መከላከያ ዐለት እንደሆነለት ይናገራል፡፡ መዝሙር 18፥2 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

የድነቴ አምላክ ከፍ ይበል

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች የድነቴን አምላክ ከፍ ያድርጉት››

የድነቴ አምላክ

‹‹ድነት›› የሚለው ስም፣ ‹‹መዳን›› ወይም፣ ‹‹መታደግ›› ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የታደገኝ አምላክ››

የሚበቀልልኝ አምላክ

‹‹የሚበቀልልኝ›› ማለት ሰዎችን በክፉ ሥራቸው የሚቀጣ ማለት ነው፡፡ ‹‹በቀል›› የሚለውን ቃል ማውጣት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ላይ ባደረጉት ክፉ ሥራ ሰዎችን የሚቀጣ አምላክ››