am_tn/psa/018/040.md

1.4 KiB

የጠላቶቼን ማጅራት ሰጠኸኝ

ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ለዳዊት ጠላቶቹ ላይ ድል እንደ ሰጠው ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጠላቶቼ ላይ ድል ሰጠኸኝ››

የጠላቶቼን ማጅራት ሰጠኸኝ

ይህም የሚያመለክተው እግዚአብሔር ለዳዊት ጠላቶቹ ላይ ድል እንደ ሰጠው ነው፡፡ 1) ዳዊት የጠላቶቹን ራስ ከአንገታቸው መቁረጥ ይችላል፣ ወይም 2) ዳዊት እግሩን ጠላቶቹ ላይ ማድረግ ይችላል፤ ወይም 3) ዳዊት ከእርሱ ሲሸሹ የጠላቶቹን ጀርባ ማየት ይችላል፡፡

የሚጠሉንን አጠፋኃቸው

‹‹የሚጠሉንን አሸነፍሁ›› ወይም፣ ‹‹የሚጠሉኝን ፈጽሞ ደመሰስሁ››

እርሱ ግን አልመለሰላቸውም

ይህ ማለት ያህዌ አልረዳቸውም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ ግን አልረዳቸውም››

ነፋስ ፊት እንዳለ ትቢያ አደቀቅኃቸው

ምን ያህል እንደ ተሸነፉ ለማሳየት የዘማሪው ጠላቶች ከትቢያ ጋር ተመሳስለዋል፡፡

እንደ መንገድ ላይ ጭቃ ረገጥኃቸው

ምን ያህል እንደ ተሸነፉ ለማሳየት የዘማሪው ጠላቶች በመንገድ ላይ ጭቃ ተመስለዋል፡፡