am_tn/psa/018/037.md

990 B

አደቀቅኃቸው

‹‹ፈጨኃቸው›› ወይም፣ ‹‹ሰባበርኋቸው››

መነሣት አይችሉም

‹‹መቆም አይችሉም››

በእግሮቼ ሥር ወደቁ

አነጋገሩ ዘማሪው ጠላቶቹን አሸነፈ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሁሉንም አሸነፍኋቸው››

ኀይልን አስታጠቅኸኝ

ዘማሪው እርሱን ለመደገፍ ወገቡ ላይ እንደሚታጠቀው ቀበቶ ያህዌ ኀይል እንደ ሰጠው ይናገራል፡፡

ከእግሬ ሥር አደረግህልኝ

እዚህ ላይ ዘማሪ የጠላቶቹ መሸነፍ እነርሱ ላይ መቆም ማለት እንደሆነ ይናገራል፤ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ አሸነፍህልኝ››

በእኔ ላይ የተነሡትን

ይህ የሚያመለክተው ዘማሪውን የሚቃወሙትን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶቼን››