am_tn/psa/018/035.md

1.6 KiB

የድነት ጋሻ

እዚህ ላይ ጸሐፊው የእግዚአብሔር ጥበቃ እንደ ጋሻ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ‹‹ድነት›› የሚለውን፣ ‹‹መዳን›› በማለት መተርጐ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጥበቃህ አዳነኝ››

ቀኝ እጅህ ደገፈኝ

የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ኀይሉን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኀይልህ ደገፈኝ›› ወይም፣ ‹‹አንተ በኀይልህ ደገፍኸኝ››

ሞገስህ ታላቅ አደረገኝ

እዚህ ላይ የእግዚአብሔር ሞገስ እንደ እርሱ ሞገስ ያደረገውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ሞገስህ ታላቅ አደረግኸኝ›› ወይም፣ ‹‹በቸርነትህ ታላቅ አደረግኸኝ››

ከእግሮቼ በታች ያለውን ቦታ አሰፋህልኝ

እግዚአብሔር ያደረገለት ጥበቃ የሚቆምበት ሰፊ ቦታ እንደ መስጠት መሆኑን ጸሐፊው ይናገራል፡፡ እዚህ ላይ፣ ‹‹እግሮቼ›› ሰውየውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለእኔ ደህና ቦታ››

እግሮቼ አልተንሸራተቱም

‹‹እግሮቼ›› ሰውየውን ይወክላል፡፡ እግዚአብሔር ያደረገለት ጥበቃ ተንሸራትቶ እንዳይወድቅ ደህና ቦታ መቆም ማለት እንደሆነ ጸሐፊው ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አልተንሸራተትሁም›› ወይም፣ ‹‹በደንብ ቆሜአለሁ››