am_tn/psa/018/030.md

1.4 KiB

ለሚጠጉት ሁሉ ጋሻ ነው

ጋሻ ወታደሩን ይከልላል፡፡ ዳዊት ያህዌ የሚከልለው ጋሻ እንደሆነ ይናገራል፡፡ መዝሙር 3፥3 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ሆይ፣ ወደ አንተ የሚጠጉትን እንደ ጋሻ ትከልላቸዋለህ››

ከያህዌ በቀር አምላክ ማነው? ከአምላካችን በቀር ዐለት ማን ነው?

የሚጠበቀው መልስ ማንም የለም የሚል ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ብቻ አምላክ ነው፤ አምላካችን ብቻ ዐለት ነው››

ዐለት

ያህዌ ከጠላቶቹ ለማምለጥ የሚወጣበት ዐለት እንደ ሆነ ዳዊት ይናገራል፡፡ መዝሙር 18፥2 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

ኀይልን አስታጠቅኸኝ

እግዚአብሔር ለዳዊት ትጥቅ የሚሆነው ኀይል ሰጠው

ቀናውን ሰው በመንገዱ አደረገ

እዚህ ላይ ዳዊት በትክክለኛው መንገድ በመሄድ ያህዌን ደስ ሚያሰኝ ሕይወት እየኖረ እንደሆነ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ቀናውን ሰው የጽድቅ ሕይወት እንዲኖር አደረገ››