am_tn/psa/018/020.md

839 B

እጆቼ ንጹሕ ነበሩ

የእጅ ንጽሕና የሚያመለክተው በደል አለማድረግን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በደል አልነበረብኝም›› ወይም፣ ‹‹ያደረግሁት ትክክል ነበር››

የያህዌን መንገዶች ጠብቄአለሁ

የያህዌ ሕጐች ሰው ሊመላለስባቸው የሚገባ መንገዶች እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለያህዌ ሕጐች ታዝዣለሁ››

በዐመፅ ከያህዌ አልራቅሁም

እዚህ ላይ ዐመፅ ትክክለኛውን መንገድ በመተው ትክክል ባልሆነው መንገድ መሄድ ማለት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከአምላኬ በመራቅ ዐላመፅሁም››