am_tn/psa/018/007.md

1.5 KiB

ያህዌ ስለ ተቆጣ… ምድር ተናወጠ

የእግዚአብሔር ቁጣ ከባድ የመሬት መናወጥ እንዳመጣ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እግዚአብሔር በጣም ስለ ተቆጣ… ምድር ተናወጠ››

ምድር ተንቀጠቀጠ ተናወጠም

‹‹መንቀጥቀጥ›› እና፣ ‹‹መናወጥ›› በመሠረቱ ተመሳሳይ ቢሆኑም፣ አጽንዖት የተሰጠው ምድር በኀይል እንደ ተንቀጠቀጠ ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምድር ወደ ፊት ወደ ኃላ ተንቀሳቀሰ›› ወይም፣ ‹‹ምድር ወደ ላይ ወደ ታች ተንቀሳቀሰ›› ወይም፣ ‹‹ከባድ የምድር መናወጥ ሆነ››

የተራሮች መሠረትም ተንቀጠቀጠ፤ ተናወጠ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የተራሮች መሠረትም ተንቀጠቀጠ ተናወጠ››

ከአፍንጫው ጢስ ወጣ… ፍም ከእርሱ ወጣ

ዳዊት ያህዌ እሳት እየተነፈሰ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ይህም እግዚአብሔር ምን ያህል እንደ ተቆጣ ያሳያል፡፡

ከአፉ የሚባላ እሳት ወጣ፤ ከእርሱም እሳት ነደደ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሚባላ እሳት ከአፉ ወጣ፤ ከዚያም እሳት ነደደ››