am_tn/psa/018/002.md

1.2 KiB

ያህዌ ዐለቴ ነው

ዳዊት ያህዌ ዐለት እንደሆነ ይናገራል፡፡ ‹‹ዐለት›› የምቹ ቦታ ምሳሌ ነው፡፡

ዐለቴ መሸሸጊያዬ

እዚህ ላይ ‹‹ዐለት›› እና፣ ‹‹መሸሸጊያ›› ተመሳሳይ ነገሮች ቢሆኑም፣ ያህዌ ከጠላት ማምለጫ ቦታ እንደሚያዘጋጅ አጽንዖት ይሰጣል፡፡

የምሸሸግበት

መከላከያ ለማግኘት ወደ ያህዌ መሄድ በእርሱ ውስጥ መሸሸግ ማለት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንድከለል ወደ እርሱ እሄዳለሁ››

ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው

ያህዌ፣ ‹‹ጋሻው›› የድነቱ፣ ‹‹ቀንድ›› እና፣ ‹‹ዐምባው›› እንደሆነ ዳዊት ይናገራል፡፡ ከጉዳት የሚጠብቀው ያህዌ ነው፡፡ እዚህ ላይ አጽንዖት ለመስጠት ተመሳሳይ ሐሳቦች በሦስት የተለያዩ መንገዶች ቀርበዋል፡፡

ከጠላቶቼ እድናለሁ

‹‹ከጠላቶቼ አመልጣለሁ››