am_tn/psa/017/013.md

1.6 KiB

ያህዌ በሰይፍም ከክፉዎች ታደገኝ … እንዲህ ካሉት ሰዎች በክንድህ አድነኝ

ሁለቱም ሃረጎች ተመሳሳይ ትርጓሜ አላቸው። መደገማቸው ትኩረትን ይጨምራል። (ትይዩነትን ይመልከቱ)

በሰይፍህ … በክንድህ

“ሰይፍ” የሚለው ቃል እና “ክንድ” የሚለው ቃል የያህዌን ኃይል ያመለክታሉ። (ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)

የመዝገቦችህን ሆዳቸውን ሙላ

የጥንቱ ጽሑፍ ለመረዳት አስቸጋሪ ነው። አማራጭ ፍቺዎች 1) “መዝገብ” ለፍቅር ቅኔያዊ መግለጫ ነው፥ ስለዚህ “መዝገብ” በእግዚአብሔር የተወደዱትን ያመለክታል። አማራጭ ትርጉም፡ “የምትወዳቸውን ሰዎች ሆድ በፍቅርህ ተሞላለህ” ወይም 2) “የመዝገቦችህ” የሚያመለክተው እግዚአብሔር ለዚህ ዓለም ህዝብ የሚሰጠውን መዝገብ ነው፥ አማራጭ ትርጉም፡ “ሆዳቸውን በሀብት መዝገብ ትሞላለህ” (ቅኔን ይመልከቱ)

የመዝገቦችህን ሆዳቸውን ሙላ

“የመዝገቦችህን ሆዳቸውን ሙላ” የሚያመለክተው ብዙ ውድ ነገሮቸን መስጠትን ነው። አማራች ፍቺዎች 1) “ለምትወዳቸው ሰዎች ብዙ ሀብትን ትሰጣቸዋለህ” ወይም 2)”ለዚህ ዓለም ሰዎች ብዙ ሀብትን ትሰጣቸዋለህ” (ቅኔን ይመልከቱ)