am_tn/psa/017/003.md

753 B

ልቤን መረመርኸው በሌሊት ጠጋ ብለህ ፈትነኸኝ

“ልቤን መረመርኸው” ማለት ሀሳቤን እና ስሜቴን መርምር ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፡ “ሀሳቤን በሌሊት ብትመረምር” (ፈሊጥን ይመልክቱ)

አንደበቴ እላፊ አይሄድም

እዚህ ጋር አንደበት በራሱ መንቀሳቀስ እንደሚችል ነው የተገለጸው። የሚወክለውም ሰው የሚናገረውን ቃላት ነው። አማራጭ ትርጉም፡ “ውሸትን አልናገርም ወይም በቃላቴ ኃጢአትን አልሰራም” (ሰውኛ ዘይቤ እና በአንድ ክፍል ሙሉ አካልን መሰየምን ይመልከቱ)