am_tn/psa/017/001.md

1.6 KiB

አጠቃላይ ሃሳብ፡

በዕብራይስጥ ቅኔ ትይዩነት የተለመደ ነው፡፡ (ቅኔ እና ትይዩነትን ይመልከቱ)

የዳዊት ጸሎት

“ይህ ዳዊት የጻፈው ጸሎት ነው”

ከአታላይ ከንፈር ያልወጣውን ጸሎቴን አድምጥ

“ጆሮ ስጥ” ስማ ለሚለው ቅኔ ነው። “ከአታላይ ከንፈር ያልወጣ” ከማይዋሽ ሰው ለሚለው ወካይ ነው። አማራጭ ትርጉም፡ “ያለሽንገላ የሆነ ጸሎቴን አድምጥ” (ቅኔን እና በአንድ ክፍል ሙሉ አካልን መሰየምን ይመልከቱ)

ጽድቄ ከአንተ ዘንድ ይምጣ

ጽድቅ ከእግዚአብሔር ዘንድ መምጣት የሚያመለክተው እግዚአብሔር ፈርዶ አንድን ሰው ጻድቅ ሲለው ነው። የእግዚአብሔር መገኘት ለእግዚአብሔር ለራሱ ገላጭ ነው። አማራጭ ተርጉም፡ “ጽድቄ ከአንተ ዘንድ ይምጣ” ወይመ “ንጹህ እንደሆነሁ ተናገር” (ቅኔ እና ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)

ዐይኖችህም ፍትህን ይዩ

ዐይኖችህ የሚወክለው እራሱ እግዚአብሔርን ነው። “ይዩ” የሚለው ሃሳብ ትኩረትን መስጠት እና አንድ ነገር ለማድረግ መወሰን ያመለክታል። አማራጭ ትርጉም፡ “አባክህ ትክክል የሆነውን ተመልከት” ወይም “ትክክል የሆነው አድርግ” (ቅኔን እና በአንድ ክፍል ሙሉ አካልን መሰየምን ይመልከቱ)