am_tn/psa/016/009.md

845 B

አጠቃላይ ሃሳብ

ዳዊት ስለ እግዚአብሔር መናገር ይቀጥላል

ልቤ ሐሴት ያደርጋል

“ልብ” የሚወክለው የተናጋሪውን ሀሳብ እና ስሜትን ነው። አማራጭ ትርጉም፡ “ስለዚህ ደስተኛ ነኝ” (ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)

ክብሬ ይደሰታል

አማራጭ ፍቺዎች 1) “ክብር” የሚለው ቃል የሚወክለው አንድ ሰው የሚሰማውን ክብር። አማራጭ ትርጉም፡ “በእግዚአብሔር በመደሰቴ ክብር ይሰማኛል” ወይም 2) “ከብር” ለሚለው ቃል የተጠቀመው የዕብራይስጥ ቃል “ጉበት” ማለት ነው፥ ይህም የሰውን ስሜት ይወክላል። አማራጭ ትርጉም፡ “ደስተኛ ነኝ”