am_tn/psa/016/005.md

1.6 KiB

የርስቴ ድርሻዬ

ዳዊት ስለ ያህዌ እንደ ተሰጠው የመሪት ድርሻ ይናገራል። (ቀኔን ይመልከቱ)

ጽዋዬ

ዳዊት ስለ ያህዌ ብዙ በረከትን እንደያዘ ጽዋ ይገልጸዋል። አማራጭ ትርጉም፡ “የሚባርከኝ” (ቀኔን ይመልከቱ)

ዕጣዬ በእጅህ ናት

“የወደፊቴን የምትወስን አንተ ነህ” ወይም “በእኔ የሚሆነውን ትቆጣተራለህ”

ገመድ ባማረ ስፍራ

ገመድ መጣል መሪትን ለመለካት እና ለሰው ለመስጠት ሌላ ስያሜ ነው። ዳዊት ከእግዚአብሔር በተለዩ ታላላቅ መንገዶች ስላገኘው በረከት ቅኔያዊ መግለጫ ነው። በቀጥታ ሊገለጥ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡ “በመልካም ስፍራ መሪት ወስነህልኛል” ወይም “በመልካም ስፍራ መሪት ሰተኸኛል” ወይም “በመልካም ስፍራ መሪት እንደሚሰጥ ባርከኸኛል” (ድጋሚ መሰየም፥ ቅኔ፥ ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪን ይመልከቱ)

ገመድ

ገመድ በዚያን ጊዜ መሪትን ለመለካት አና ድንበር ለመከለል ይጠቀሙበት ነበር።

በርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ

ዳዊት የያህዌን በረከት እንደተቀበለው ርስት አድርጎ ይገልጸዋል። አማራጭ ትርጉም፡ “በሰጠኝ ነገር ሁሉ ደስተኛ ነኝ” (ቀኔን ይመልከቱ)