am_tn/psa/016/001.md

1.1 KiB

አጠቃላይ ሃሳብ፡

በዕብራይስጥ ቅኔ ትይዩነት የተለመደ ነው፡፡ (ቅኔ እና ትይዩነትን ይመልከቱ)

የዳዊት ቅኔ

ቅኔ በሚለው ፋንታ ያለው የዕብራይስጡ ቃል ትርጉም በእርግጠኝነት አይታወቅም። በምትኩ “መዝሙር” ወይም “ቅኔ” የሚለውን ቃል መጠቀም ይቻላል። እንዲህ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡ “ይህ መዝሙር ዳዊት የጻፈው ነው”

መጠጊያዬ ነህ

ለመሸሸግ ወደ ያህዌ መሄድ እርሱን መጠግያ እንደ ማድረግ ይገለጻል። አማራጭ ትርጉም፡ “ለመሸሸግ ወደ አንተ እመጣለሁ” (ቅኔን ይመልከቱ)

በምድር ያሉ ቅዱሳን ሁሉ

“ቅዱሳን” የሚወክለው በእርሱ የሚታመኑትን የእግዚአብሔር ሕዝብን ነው። አማራጭ ትርጉም፡ “በዚህ ምድር የሚኖሩ ሕዝብህ” (ግምታዊ እውቀትን እና ድብቅ ሃሳብ ይመልከቱ)