am_tn/psa/010/008.md

854 B

ያደፍጣል

ይህ ድርጊት በክፉው ሰው ይደረጋል።

ዐይኖቹ በምስኪኖች ላይ ያነጣጥራል

ዐይኖቹ እርሱን ይወክላሉ። አማራጭ ትርጉም፡ “ረዳት የሌላቸው ምስኪኖችን ይመለከታል” (በአንድ ክፍል ሙሉ አካልን መሰየምን ይመልከቱ)

በደኑ ውስጥ እንዳለ አንበሳ በስውር ያደባል

ይህ ሃሳብ ክፉው ሰው ልክ እንደ አንበሳ ይገልጸዋል። አማራጭ ትርጉም፡ “ደካሞች እስቀሚቀርቡት ድረስ አንበሳ እንስሳን ለማጥቃት በዝምታ እንደሚያደባ ይደበቃል” (አነጻጻሪ ዘይቤን ይመልከቱ)

ያደባል

ለመጉዳት ወይም ለመግደል ተደብቆ መቆየት ማለት ነው።