am_tn/psa/009/015.md

1.4 KiB

አሕዛብ በቆፈሩት ጉድጓድ ገቡ

ሰዎች እንስሳትን ለማጥመድ ጉድጓድ ይቆፍራሉ። እዚህ ጋር ጉድጓድ መቆፈር ሰዎችን ለማጥፋት ማቀድን ይወክላል። አማራጭ ትርጉም፡ “አሕዛብ ለሉሎች ጉድጓድን ይቆፍራሉ እራሳችው ይገቡበታል” (ቅኔን ይመልከቱ)

እግቸውም እራሳቸው በስውር ባስቀመጡት ወጥመድ ተያዘ

ሰዎች እንስሳትን ለማጥመድ ወጥመድ ይዘረጋሉ። እዚህ ጋር ወጥመድ በስውር ባስቀመጥ ሰዎችን ለማጥፋት ማቀድን ይወክላል። አማራጭ ትርጉም፡ “በደበቁት ወጥመድ እንደሚያዙ ሰዎች ናቸው” (ቅኔን ይመልከቱ)

ክፉዎች በእራሳቸው ስራ ተጠመዱ

እዚህ ጋ ክፉዎች የሚለው ቃል ማንኛውም ኃጢአተኛ ሰውን ይወክላል። አንድ ክፉ ሰው ሌላ ሰውን ለመጉዳት የሚሰራ ስራ ሌሎች እንዲያዙበት ወጥመድ እንደማዘጋጀት ተገልጧል። ይህ በቀጥተኛ መንገድ ሊገለጥ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡ “አንድ ክፉ ሰው ሌሎች ሰዎችን ለመጉዳት ሲሞክር፥ የእራሱ ስራ መልሶ ይጎዳዋል”

ተጠመዱ

“ወጥመድ ውስጥ ገቡ”