am_tn/psa/009/007.md

1.2 KiB

ያህዌ ለዘላለም ይኖራል

“ይኖራል” የሚለው ቃል የሚወክለው በዙፋኑ እንደ ንጉሥ መኖርን ነው። አማራጭ ትርጉም፡ “ያህዌ ለዘላለም በዙፋኑ ይቀመጣል” ወይም “ያህዌ ለዘላለም ይገዛል” (ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)

መንበሩንም ለፍርድ አፍንቶአል

“መንበሩ” የሚለው ቃል ዙፋኑን ወይም አገዛዙን ይወክላል። አማራጭ ፍቺ 1) “በሰዎች ለመፍረድ ይገዛል” ወይም “በጽድቅ በሰዎች ላይ ይገዛል” (ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)

በዓለም በጽድቅ ይፈርዳል … በፍትህ በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል

እነዚህ ሁለት ሃረጎች ተመሳሳይ ሃሳብ አላቸው (ትይዩነትን ይመልከቱ)

በጽድቅ በዓለም ላይ ይፈርዳል

“ዓለም” የሚለው ቃል እዚህ ጋር የሚወክለው በዓለም ያሉትን ሰዎች ነው። አማራጭ ትርጉም፡ “በጽድቅ በዓለም ያሉትን ሰዎች ሁሉ ላይ ይፈርዳል” (ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)