am_tn/psa/008/003.md

1.1 KiB

ጣቶችህ ያመጁት ሰማያትህ

የእግዚአብሔር ጣቶች እርሱን ይወክላሉ። አማራጭ ትርጉም፡ “አንተ የሰራሃቸው ሰማያት”

በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?

እነዚህ ሃሳቦች ትኩረትን ለመስጠት በጥያቄ መልክ ተቀምጠዋል። አማራጭ ትርጉም፡ “ሰለሰዎች ማሰብህ እና መጠንቀቅህ አስገራሚ ነው!” (መልስ አዝል ጥያቄን ይመልከቱ)

የሰው ዘር…. የሰው ልጅ

ሁለቱም ሃረጎች በአጠቃላይ ሰዎችን ይወክላሉ።

የክብር እና የሞገስ ዘውድ ደፋህላቸው

ክብር እና ሞገስ እንደ ዘውድ ተገልጸዋል። ‘ክብር’ እና ‘ሞገስ’ የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ፍቺ አላቸው። አማራጭ ትርጉም፡ “ክብር እና ሞገስ ሰጥተሃቸዋል” ወይም “እንደ ንጉሥ እንዲሆኑ እድርገሃቸዋል” (ቅኔ እና መድገምን ይመልከቱ)