am_tn/psa/008/001.md

1.6 KiB

አጠቃላይ ሃሳብ

ትይዩነት በዕብራይስጥ ቅኔ የተለመደ ነው (ቅኔ እና ትይዩነትን ይመልከቱ)

ለመዘምራን አለቃ

“ይህ ለመዘምራን አለቃ ለአምልኮ እንዲጠቀምበት ነው”

በዋሽንት

“ይህ መዝሙር በዋሽንት በሚጠቀሙ መታጀብ አለበት”

የዳዊት መዝሙር

አማራጭ ፍችዎች፡ 1) ዳዊት ዝማሬውን ጽፎታል ወይም 2) ዝማሬው ስለዳዊት ነው ወይም 3) ዝማሬው የተዘመረው በዳዊት የአዘማመር ስልት ነው፡፡

ስምህ በምድር ላይ እንዴት ታላቅ ነው

የእግዚአብሔር ስም ማንነቱን ይወክላል። አማራጭ ትርጉም፡ “በምድር ያሉ ሰዎች ሁሉ ታላቅነትህን ያውቃሉ” (ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)

ከሕጻናት እና ከሚጠቡ አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ

አማራጭ ፍችዎች 1) ምስጋና እንደ ቁስ አካል ተገልጧል። እግዚአብሔር ከህጻናት እና ከሚጠቡ አፍ ያወጣው እና እንደ መከላከያ ግንብ ያኖረዋል ወይም 2) እግዚአብሔር አለምን የፈጠረው ምስጋና ህጻናት አንደበት እንዲወጣ ነው። አማራጭ ትርጉም፡ “ለህጻናት እና ለሚጠቡ አንተን የማመስገን ብቃት ሰጥተሃቸዋል” ወይም “በእውነት የሚያመሰግኑህ ህጻናት እና የሚጠቡት ናቸው” (ቅኔን ይመልከቱ)