am_tn/psa/007/006.md

1.9 KiB

እግዚአብሔር ሆይ በቁጣህ ተነስ

መነሳት እንድን ነገር ማድረግ ወይም እርምጃ መውሰድን ያመለክታል። አማራጭ ትርጉም፡ “በቁጣህ አንድ ነገር አድርግ” ወይም “በጠላቶቼ ላይ ተቆጣ እና እርምጃ ውሰድ” (ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)

በቁጣ በተነሱብኝ ላይ ተነስ

ከሰዎች ጋር መጣላት ወይም መዋጋት በእነርሱ ላይ እንደ መነሳት ይገለጻል። አማራጭ ትርጉም፡ “በቁጣ የሚዋጉኝን ተዋጋቸው” ወይም “የተቆጡኝ ጠላቶች አጥቃቸው” (ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)

የጠላቶቼ ቁጣ

የጠላቶች ቁጣ ማጥቃታቸውን ያመለክታል። አማራጭ ትርጉም፡ “የጠላቶቼ ጥቃት” ወይም “የሚያጠቁኝ ጠላቶቼ” (ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)

ተነስ

መነሳት አንድ ነገር ማድረግ መጀመር ወይም እርምጃ መውሰድ ያመለክታል። አማራጭ ተርጉም፡ “እርምጃ ውሰድ ” ወይም “አንድ ነገር አድርግ” (ቅኔን ይመልከቱ)

ስለ እኔ ስትል

“ለእኔ” ወይም “እኔን ለመርዳት”

አገሮች ተሰባሰቡ

አገር የሚለው ቃል የሚወክለው ለማጥቃት የተሰባሰቡትን ጦሮችን ነው

በእነርሱ ላይ ለአንድ ጊዜ የሚገባህን ስፍራ ውሰድ

ሰዎችን መግዛት በእነርሱ ላይ እንደመሆን ይገለጻል። የያህዌ የሚገባ ስፍራ ሰማያትን ወይም በአጠቃላይ መግዛትን ያመለክታል። አማራጭ ትርጉም፡ “ከሰማይ በእነርሱ ላይ ግዛ” ወይም “በእነርሱ ላይ ግዛ” (ቅኔን ይመልከቱ)